ቶተንሀም ሆትስፐር አንጂ ፖስቴኮግሉን አሰናበተ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐር የክለቡን አሰልጣኝ አንጂ ፖስቴኮግሉን አሰናብቷል፡፡
አሰልጣኙ በስፐርስ በነበራቸው የሁለት ዓመት ቆይታ የዩሮፓን ሊግ ዋንጫን አሳክተዋል፡፡
በፖስቴኮግሉ የተመራው ቶተንሀም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ደካማ የውድድር ጊዜ አሳልፏል፡፡
በሊጉ ካደረጋቸው 38 ጨዋታዎች በ22ቱ ተሸንፎ፤11 ጨዋታ አሸንፎ በ5 ጨዋታዎች ደግሞ አቻ መለያየቱ አይዘነጋም፡፡
ውጤቱን ተከትሎም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 38 ነጥብ በመሰብሰብ 17ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡
አሰልጣኝ አንጂ ፖስቴኮግሉ ዩሮፓ ሊግን በማሸነፍ ቶተንሀምን ከ17 ዓመታት በኋላ ከዋንጫ ጋር ማገናኘት ቢችሉም፤ በፕሪሚየር ሊጉ ቡድኑን ውጤታማ ማድረግ ባለመቻላቸው ወቀሳ በርትቶባቸው ነበር፡፡