Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባደረጉት ባለ አራት ክፍል ቃለ ምልልስ በክፍል ሦስት፤ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-

👉 የኢትዮጵያን ሰው፣ መሬት እና ሀብት ከጫፍ እስከ ጫፍ ደምረን መጠቀም አለብን።

👉 በደቡብ ኦሞ 145 ኪሎ ሜትር መስኖ ሠርተናል፤ ይህን በአግባቡ በማሽን ታግዞ መጠቀም ሀገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን ያሳልጣል፡፡

👉 ቆላ ማለት ብዙን ድርሻ የያዘው የኢትዮጵያ ክፍል ነው፤ በማሽን በቀላሉ መልማት እና ብዙ ምርት መስጠት የሚችል አካባቢ ነው፡፡

👉 አጋር (ሁለተኛ ዜጋ) የተባለውን ሠርዘን፤ ባለቤት እንዲሆን አድርገናል፤ መሬቱን ብቻ ሳይሆን ሰውንም ደምረነዋል፡፡

👉 ኢትዮጵያ በአፍሪካ አንደኛዋ ስንዴ አምራች ናት፤ ሁለተኛ አምራቿን ግብጽንም በሦስት እጥፍ ትበልጣታለች፡፡

👉 ምን ያህል መሬት እንደታረሰ በየአካባቢው ሂደን ማየት አይጠበቅብንም፤ ባለንበት ቦታ ሆነን በሳተላይት ምስል እንመለከታለን፡፡

👉 ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት በመጣሁ ሰሞን እስከ 1 ቢሊየን ዶላር ስንዴ ከውጭ ለማስገባት ይወጣ ነበር፤ ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመት ግን አንድ ብር ስንዴ ለማስገባት አላወጣንም፡፡

👉 ኢትዮጵያ በርካታ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞችን እንደመያዟ የሚረዱ አካላት ስንዴ ሊልኩ ይችላሉ፤ ይህ ግን ለኢትዮጵያ የተላከ ዕርዳታ አይደለም፤ ለስደተኞች እንጂ፡፡

👉 የነቃ አስተሳሰብ ቅድሚያ ለሀገር ምርት ይሰጣል፤ ችግር ቢኖር እንኳ በሀገር ምርት መኩራት ይገባል፡፡

👉 የገበያ ሥርዓቱ ድክመት አለበት፤ በዚህም ድሃው እንዳይጎዳ መንግሥት በትኩረት እየሠራ ነው፡፡

👉 ምርታማነታችንን በሔክታር ለማሳደግ በቀጣይ መሥራት ይጠበቃል።

👉 በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ቆላ ላይ ከፍተኛ ሐብት አላት፤ የከርሰ እና ገጸ ምድር ውኃው፣ የዝናቡ ሁኔታ፣ ያልታረሰ መሬት መኖሩ … በቀጣይ አበክረን መሥራት አለብን፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.