የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ፖርቹጋል ከስፔን ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት የፍጻሜ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሙኒክ አሊያንዝ አሬና ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን÷ ሁለቱ ቡድኖች ካላቸው ምርጥ ተጫዋቾች አንጻር አጓጊ ሆኗል፡፡
በፖርቹጋል በኩል የ40 ዓመቱ ክሪስቲያኖ ሮናልዶን ጨምሮ ቪቲኒሃ፣ ጆዓዖ ኔቬስ የመሳሰሉ ከዋክብቶች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚጠበቅ ሲሆን÷ በስፔን በኩል የባርሴሎና ኮከቦች ላሚንያማል፣ ፔድሪን የመሳሳሉ ተጫዋቾች ይጠበቃሉ፡፡
በኔሽንስ ሊጉ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፖርቹጋል ጀርመንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜው ማለፍ ስትችል÷ ስፔን በበኩሏ ፈረንሳይን 5 ለ 4 በሆነ ውጤት አሸንፋ ነው የፈጻሜ ተፋላሚ የሆነችው፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ ጀርመን እና ፈረንሳይ 3ኛ ደረጃን ይዘው ለማጠናቀቅ ይፋለማሉ፡፡