Fana: At a Speed of Life!

18ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መነሻውንና መድረስ በመስቀል አደባባይ ያደረገው 18ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ፋንቱ ወርቁ እና በወንዶች ሌሊሳ ፉፋ አሸንፈዋል።

ውድድሩን በሴቶች ፋንቱ ወርቁ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በበላይነት ስታጠናቅቅ÷ ውድድሩን ለመጨረስ 1 ሰዓት ከ13 ደቂቃ 30 ሴኮንድ ወስዶባታል።

በውድድሩ ዓይንዓለም ደስታ ከመቻል 2ኛ ስትወጣ÷ ብዙአገር አደራ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3ኛ በመውጣት አጠናቃለች።

በወንዶች ሌሊሳ ፉፋ 1 ሰዓት 03 ደቂቃ 46 ሴኮንድ በመግባት ከኦሮሚያ ፖሊስ በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል።

ነጋሳ ደቀባ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን 2ኛ ስወጣ÷ ሰይፉ ቱራ በግል 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

በውድድሩ ለአሸናፊ አትሌቶች የ150 ሺህ ብር ሲበረከትላቸው÷ 2ኛ ለወጡት የ100 ሺህ ብር እንዲሁም 3ኛ ለወጡት የ75 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.