Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከ70 ሺህ ቶን በላይ ማር ተመረተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለፉት 10 ወራት ከ70 ሺህ ቶን በላይ ማር ተመርቷል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የንብና ሐር ልማት ባለሙያ አቶ አገኘሁ በላቸው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት፤ የሌማት ቱርፋት መርሐ ግብር ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ ከ900 በላይ የንብ መንደሮች በክልሉ ተመስርተዋል።

ይህም ቀደም ሲል ከነበረው 50 ሺህ ቶን ማር የማምረት አቅም ወደ 70 ሺህ ቶን እንዲያድግ ማስቻሉን ጠቁመዋል።

በ2017 በጀት ዓመት ከ71 ሺህ ቶን በላይ ማር ለማምረት ያቀደው ክልሉ በ10 ወራት ውስጥ 70 ሺህ 900 ቶን ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።

የማር ምርታማነትን በክልሉ ለማሳደግ በቀጣይ ራሱን የቻለ የንብ ማነብ ኢንሼቲቭን ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ጠቁመዋል።

በተስፋዬ ምሬሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.