Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለድህነት ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል አለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢኮኖሚ ማሻሻያው በድህነት ቅነሳና አምራች ዘርፉን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል አለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ለማጠናከር ያለመ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በዚሁ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አማካሪ አምባሳደር ወርቃለማሁ እንዳሉት፤ የኢኮኖሚ ማሻሻያው በድህነት ቅነሳ፣ የግሉን ዘርፍ እና አምራች ዘርፉን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል።

በተጨማሪም የንግድ ችግሮችን እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን በመቅረፍ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ማድረጉን ገልፀዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ በውጭ የቀጥታ ኢንቨስትመንት ከቀጣናው ቀዳሚ ከአፍሪካ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃ እንድትይዝ አስችሏል ነው ያሉት።

በገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዘርፍ አማካሪ አልባብ አብደላ በበኩላቸው፤ የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኢንሼቲቮች የራሱን አስተዋፅኦ ማበርከቱን ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያዊ የደቡብ ለደቡብ እና የብሪክስ ፕላስ አባል መሆኗ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት ዕድል መፍጠሩንም ጠቁመዋል፡፡

ከዓለም ተለይቶ ማደግ አይቻልም ያሉት አማካሪው፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ኢትዮጵያያሏትን ዕድሎች ከውጩ ዓለም ጋር ያስተሳሰረችበት ነው ብለዋል፡፡

ማሻሻያው ከቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት እንዲሁም ብድር ለማስተካከል ከፍኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን አብራርተዋል።

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.