ሙሉጌታ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከምንጊዜም ምርጥ ኢትዮጵያውያን የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ሙሉጌታ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ሙሉጌታ ከበደ ባጋጠመው ህመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ሕይወቱ አልፏል፡፡
ሙሉጌታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ለበርካታ ዓመታት በድንቅ ብቃት ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ በነበረው ቆይታ አምበል ሆኖም መጫወት የቻለ ድንቅ ተጫዋች ነበር።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ለበርካታ ዓመታት በመጫወት የሚታወቀው ሙሉጌታ ከበደ (ወሎየዉ) ባጋጠመው ህመም ምክንያት በህክምነ ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል።
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር በነገው ዕለት የሚፈጸም መሆኑን ቤተሰቦቹ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
በ1970 እና 80ዎቹ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ በኮከብነት ያበራው አንጋፋው ሙሉጌታ ከበደ በኢትዮጵያ እግር ኳስ እስካሁን ከታዩት ድንቅ ተጫዋቾች አንዱ ነበር።