የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ በ2017 በጀት ዓመት የስኳር እና ኢታኖል ምርት ለገበያ በማቅረብ 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ።
ፋብሪካው ዓመታዊ የስኳር ምርቱን 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል እንዲሁም የኢታኖል ምርቱን 20 ሚሊየን ሊትር ለማድረስ አቅዶ እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል።
የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ኃይለማርያም ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት፤ ፋብሪካው የማምረት አቅሙን ለማሳደግ የሚያስችሉ ማሽኖችን እየተከለ ይገኛል።
በተያዘው በጀት ዓመት 383 ሺህ ኩንታል ስኳር እንዲሁም 4 ነጥብ 7 ሚሊየን ሊትር ኢታኖል ያመረተው ፋብሪካው፤ ምርቱን ለገበያ በማቅረብ 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር አግኝቷል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት 19 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ አገዳ መተከሉን ገልጸው፤ ይህንን አቅም ወደ 21 ሺህ ሄክታር ከፍ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።
ፋብሪካው በተለያየ ምክንያት ጉዳት በማስተናገዱ ለማገገም ስትራተጂክ ዕቅድ ነድፎ ምርታማነቱን ለማሳደግ እየሰራ ነው ብለዋል።
መንግስት ስኳር ፋብሪካዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረትም ከስኳር እና ኢታኖል ምርት ባሻገር በግብርና ዘርፍ በመሰማራት የገቢ ማሳደግ እና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
ፋብሪካዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ መወሰኑ የማምረት አቅምን በማሳደግ ትርፋማ የሚያደርግ መሆኑን ዋና አስኪያጁ ገልጿል።
በገላና ተስፋ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!