በኦሮሚያ ክልል 117 ሚሊየን የሻይ ቅጠል ችግኞች ይተከላሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 117 ሚሊየን የሻይ ቅጠል ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሠራ ነው አለ።
በመርሐ ግብሩ አርሶ አደሮች እና ባለሃብቶች ባልተለመዱ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ዕድል መመቻቸቱን የገለጹት የቢሮው ኃላፊ ጌቱ ገመቹ፤ ባለሃብቶች በሻይ ቅጠል ምርት በስፋት እንዲሳተፉ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
ዘርፉ በኢኒሼቲቭ መልክ ተቀርጾ ወደ ሥራ ከተገባ በኋላ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡
በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 117 ሚሊየን የሻይ ቅጠል ችግኞችን በ7 ሺህ ሔክታር ላይ ለመትከል ታቅዶ እየተሠራ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡
በዮናስ ጌትነት