በ35ኛ ሣምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብሮች ላይ ማሻሻያ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሣምንት መርሐ ግብር የክለቦች ውጤት እና የመጫወቻ ሜዳዎች ያሉበትን ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ማሻሻያ ተደርጓል አለ፡፡
በዚህም መሠረት እሁድ ሊደረጉ የነበሩ የሊጉ ጨዋታዎች ቀደም ብለው ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲደረጉ ተወስኗል፡፡
በማግስቱ እሁድ ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ ነጥባቸው ከ39 በታች የሆኑ ሦስት ክለቦች ጨዋታዎችን በተመሳሳይ ሠዓት በተለያዩ ሜዳዎች ያደርጋሉ ነው የተባለው፡፡
የሊጉ 35ኛ ሣምንት ቀሪ ጨዋታዎች ሰኞ እና ማክሰኞ በወንጂ ሁለገብ ስታዲየም እንደሚቀጥሉም ተጠቁሟል፡፡
በሌላ በኩል የ34ኛ ሣምንት ቀሪ ጨዋታዎችን ውጤት መሠረት በማድረግ ተጨማሪ አራተኛ ሜዳ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ተመላክቷል፡፡