የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ቀጣናውን ተጠቃሚ ያደርጋል – ቴር ማጆክ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጁባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣ ልማት እና ጸጥታ ጥናት ተቋም ተመራማሪ ቴር ቶንጊክ ማጆክ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የሀገሪቱን ልማት ከመደገፍ ባሻገር የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን ተጠቃሚ ያደርጋል አሉ።
ቴር ማጆክ (ዶ/ር) በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን “ሰሃት ሂዋር” ከተሰኘው አረብኛ ዝግጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።
በጥያቄው መመለስ ከኢትዮጵያ ባሻገር የንግድ ልውውጥን ማቀላጠፍን ጨምሮ የተለያዩ ዕድሎች የሚፈጠርላቸው የቀጣናው ሀገራት ጥያቄው ምላሽ የሚያገኝበትን ሁኔታ መደገፍ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የባህር በር ጥያቄው የቀጣናው ሀገራት የሚጠቀሙበት ጉዳይ መሆኑን ለማስጨበጥ ስትራተጂ ነድፎ መስራት እንደሚገባ ገልጸው፤ በጥያቄው ላይ የተሻለ መረዳት እና መግባባት ሊኖር እንደሚገባ አመልክተዋል።
የጥያቄው መመለስ የሥራ ዕድልን የሚያሰፋ፣ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር እንዲሁም ደግሞ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል የመሰረተ ልማት ግንባታን እና የንግድ ልውውጥን የሚያሳድግ በመሆኑ በቅንጅት እና በትኩረት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የባህር ላይ ዘራፊዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ማህበረሰብ አካል መሆን እንደሚገባት ገልጸው፤ መርከቦች ያለባቸውን የመንቀሳቀስ ስጋት ለመፍታት ኢትዮጵያ የላቀ ሚና የመጫወት አቅም እንዳላት አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር ተሳትፎና አቅም የሚያጠናክር እንደሚሆን ጠቅሰው፤ በሰላም ማስከበር ውስጥ የምታደርገው ተሳትፎ የባህር ላይ ኮሪደሮችን በማስጠበቅ ረገድ ያላትን ሚና ያጎለብታል ብለዋል።
በኑርሁሴን አብዱልሃፊዝ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!