አሰባሳቢ ትርክቶችን ይበልጥ ለማስረጽ የጋራ ማንነት ግንባታ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል – ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሚዲያና የኮሙኒኬሸን ባለሙያዎች አሰባሳቢ ትርክቶችን ለማስረጽ በትኩረት መስራት ይጠበቅባቸዋል አሉ በብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)።
”የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀትና በእውነት” በሚል መሪ ሀሳብ ለአፋር ክልል አመራሮችና የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በሰመራ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት አሰባሳቢ ትርክቶችን በማስረጽ እንዲሁም የጋራ በሆኑ ማንነቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።
በዚህም ህብረ ብሔራዊ ለሆነው የአንድነት ጉዞ የጸና መሰረት ማኖር መቻሉን ጠቁመው÷ በድህረ እውነት ዘመን የጋራ ወንድማማችነትን በሚያሳደጉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በለውጡ ዓመታት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
በብልጽግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን በበኩላቸው ÷ ባለፉት ሰባት ዓመታት ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የማጠናከር ሥራ መከናወኑን አስታውሰዋል፡፡
የሚዲያና የኮሙኒኬሸን ባለሙያዎች የጋራ ትርክትን ማስረጽ ላይ በትብብር እና በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!