Fana: At a Speed of Life!

የቢሾፍቱ ከተማ የኮሪደር ልማት የደረሰበት ደረጃ የሚበረታታ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቢሾፍቱ ከተማ የኮሪደር ልማት እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ የተከናወነው ስራ የሚበረታታ ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባዋ ከቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ጋር በዛሬው ዕለት በከተማዋ እየተከናወነ ያለው ኮሪደር ልማት ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ወደ ሌሎች ከተሞች ተስፋፍቶ ህዝቡን ተጠቃሚ እንዲያደርግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተሰጠን ተልዕኮ መሰረት የቢሾፍቱ ኮሪደር ልማት የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረን ተመልክተናል ብለዋል።

ከንቲባዋ በዚሁ ወቅት፥ በመዲናዋ በኮሪደር ልማት ስራ የተገኘውን ስኬት በቢሾፍቱ ለመድገም በትብብር እንሰራለን ማለታቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የኦንላይን ሚዲያ አስተዳደር ዳይሬክተር ብሩክሰው ይልማ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

ስራው ተጀምሮ እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ያከናወነው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው፥ ቀሪ ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ በትብብር እንደሚሰራም አንስተዋል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ እንዲፋጠን የከተማዋ ነዋሪዎች እያደረጉት ላለው ትብብር ከንቲባዋ ምስጋና ማቅረባቸውንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.