የስማርት ከተሞች መመስረት የአገልግሎት አሰጣጥን አሳድጓል – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የስማርት ከተሞች መመስረት የአገልግሎት አሰጣጥን አሳድጓል አሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፡፡
መሰረተ ልማት ስለ ኢትዮጵያ የፓናል ውይይት በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሯ እንደገለፁት፤ ለመሰረተ ልማት ዝርጋታና ከተሞችን ለማዘመን ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።
በተለይም የስማርት ከተሞች መመስረት የአገልግሎት አሰጣጥን በማሳደግ የዜጎችን እርካታ ማጎልበት እንዳስቻለ ተናግረዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው፤ 92 ሚሊየን ዜጎችን የቴሌኮም እንዲሁም 52 ሚሊየን ዜጎችን ደግሞ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ አያሌው (ኢ/ር) ባለፉት ሰባት ዓመታት 26 ሺህ ኪሎ ሜትር የነበረው የመንገድ መሰረተ ልማት ወደ 75 ሺህ ኪሎ ሜትር ማሳደግ መቻሉን ገልፀዋል።
በሀገሪቱ ያለው እምቅ የኢነርጂ ሀብት ጥቅም ላይ ለማዋል በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ ሱልጣን ወሊ (ኢ/ር) ናቸው።
በተለይም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች በታዳሽ ኢነርጂ ተደረሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በውይይት መድረኩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የፌደራልና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በተስፋዬ ኃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!