Fana: At a Speed of Life!

ኬኛ ቤቬሬጅስ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ ዕድል ይዞ የመጣ ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ኬኛ ቤቬሬጅስ ኩባንያ ከኢኮኖሚ ጠቀሜታው ባሻገር በማህበራዊ ዘርፎችም በርካታ ዕድሎችን ይዞ የመጣ ነው አሉ።

በጊንጪና አካባቢው አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመፍጠር የኢንዱስትሪና የዕውቅት ማዕከል በመሆን ለአካባቢው ወጣቶች ትልቅ የስራ ዕድል ይፈጥራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በዚህና ሌሎች ምክንያቶች ኩባንያው ሕዝብን ማዕከል ያደረገ መሆኑን ገልጸው፤ ማህበረሰቡ የመጣለትን ልማት መጠበቅ እንዳለበት አመልክተዋል።

ኩባንያውም በአካባቢው ማህበራዊ ኃላፊነቶችን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው፤ በለውጡ ዓመታት መንግስት የህዝቡን አኗኗር ለማሻሻል የሚያስችሉ በርካታ ሥራዎችን ሰርቷል ብለዋል፡፡

ኬኛ ቤቬሬጅስ ጅምር ሥራ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ብዙ ቀሪ ሥራዎች እንዳሉ ገልጸዋል።

መንግስት እየተገበራቸው ያሉ ሥራዎች ህዝብን በዘላቂ ልማት ውስጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችሉ እንደሆኑም አብራርተዋል።

በዛሬው ዕለት በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ተመርቆ የተከፈተው ኬኛ ቤቬሬጅስ ኩባንያ ከ22 ቢሊየን ብር በላይ ኢንቨስትመንት በ110 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባ ነው።

በዓመት ከ3 ሚሊየን ሄክቶ ሊትር በላይ ማምረት የሚችለው ኩባንያው፤ በቴክኖሎጂ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን ይችላል።

ኩባንያው ከ4 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ባለ አክሲዮኖች፣ የህብረት ሥራ ማህበራትና ድርጅቶች በአንድ በመጣመር የሀገርን አቅም ያሳየ ሀገር በቀል ኩባንያ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፤ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር ለ1 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

በመራኦል ከድር

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.