Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኮሮናን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለዞንና ልዩ ወረዳዎች የፓርቲው ፅ/ቤቶች አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኮሮናን ለመከላከል የሚረዱ የንጽህና መጠበቂያ እና የህክምና ቁሳቁሶችን ለዞንና ልዩ ወረዳዎች የፓርቲው ፅህፈት ቤቶች አበረከተ፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው በክልሉ 16 ዞኖችና 7 ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ናቸው ተብሏል፡፡

ለፓርቲው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች የተበረከቱት ቁሳቁሶችም 25 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ማስክ፣ 14ዐ ሊትር ሳኒታይዘርና 23 የሙቀት መለኪያ መሣሪያዎች ናቸው፡፡

የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ የሀብት ልማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበበ ኤርቲሮ እንደገለፁት የአፍ መሸፈኛ ማስክ፣ ሳንታይዘርና ሙቀት መለኪያ መሣሪዎች ለቅርንጫፎቹ ተከፋፍለዋል፡፡

ለእነዚህ ቁሣቁሶችም 1 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጪ መደረጉን ገልፀው መሰል ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቻን ከክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.