Fana: At a Speed of Life!

ሠራዊቱ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እውን እንዲሆን ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ እውን እንዲሆን ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ይገኛል አሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ።

የሕዳሴ ኮር ሦስተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል “ሕዳሴን በሕዳሴ ኮር ” በሚል መሪ ሐሳብ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ እየተከበረ ነው።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት ፥ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ሃብት ነው።

መከላከያ ሠራዊት ለታላቁን ሕዳሴ ግድብ ሁሉን አቀፍ ስኬት የበኩሉን መወጣቱን አንስተው÷ የግድቡን ደህንነት ከማስጠበቅ አኳያም ታላቅ ሥራ ማከናወኑን ተናግረዋል።

ሠራዊቱ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እውን እንዲሆን በጀግንነት ደህንነቱን በማስጠበቅ ተልዕኮውን መፈጸሙን ገልጸዋል።

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት በተግባር የታየበት መሆኑን ጠቁመው ÷ ሠራዊቱ ኢትዮጵያ እንድትሻገር የሚያበረክተውን ሁሉን አቀፍ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ እና የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌ/ጄ መሠለ መሰረት ተገኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.