Fana: At a Speed of Life!

በሕንድ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜን ሕንድ ኡታራክሃንድ ግዛት ዛሬ በተከሰተ የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

አደጋው ሄሊኮፕተሩ መብረር ከጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ መከሰቱን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

በዚህም በሒንዱ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደም ጉፕካሽ ተብሎ ወደሚጠራ ኣካባቢ ሲያቀኑ የነበሩ ሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

ንብረትነቱ የአርያን አቪዬሽን የሆነው ሄሊኮፕተር በመጥፎ አየር ንብረት ሳቢያ መከስከሱ ነው የተገለጸው፡፡

በሕንድ የዛሬው አደጋ ያጋጠመው 242 መንገደኞችን አሳፍሮ ከሕንድ አሕመዳባድ ወደ ለንደን ሲበር የነበረ አውሮፕላን ተከስክሶ የ270 ሕይወት ካለፈ ሶስት ቀናት ቆይታ በኋላ ነው፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.