Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የተገነባውን የሕክምና ማዕከል መረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ የተሰኘ የሕክምና ማዕከልን በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት ÷ የሕክምና ማዕከሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ እና በአይነቱ ልዩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ ከሀገር ውጪ ሕክምና ለማገኘት የሚያጋጥሙ ወጪዎችን በመቀነስ በኢትዮጵያ ጤና ሥርዓት በርካታ እሴቶችን እንደሚጨምርም አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የአጥንት መሳሳት መመርመሪያ እንዳለው መግለጻቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ሚኤሳ ኤሌማ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በአፍሪካ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነ የልብ፣ የአንጎል እና በሰውነት ላይ የሚከሰቱ የደም ስር ችግሮችን ያለ ቀዶ ሕክምና መስራት የሚያስችል ሰው ሰራሽ አስተውሎት እንደተገጠመለት ተመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.