Fana: At a Speed of Life!

ኪነ ጥበብ ለሀገር ማንነት እና እድገት ቁልፍ ሚና ይጫወታል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ የጥበቡ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ጥበባት ለሀገር ማንነት እና እድገት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ አንስተዋል፡፡

ባሕላዊ ሃብትን ጠብቀው የሚያቆዩ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

ጥበባት ለማኅበራዊ አንደነት አበክረው በመስራት ብዝኃነት ላላቸው ማኅበረሰቦች ድምጽ ይሆናሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ በትምህርት ረገድ ፈጠራንና ምክንያታዊ አስተሳሰብን እንድሚያሳድጉ ጠቅሰዋል።

በተጨማም ከኢኮኖሚ አንጻር ጥበባት ፈጠራን፣ ቱሪዝምን እና ሥራ ፈጠራን የመምራት አቅም እንዳላቸው ነው ያስገነዘቡት፡፡

ተወካዮቹ በተለያየ ደረጃ እየተካሄደ በመጣውና በዘርፉ ያሉ ቁልፍ ጉዳዮችን ለመለየት በረዳው ሰፊ የውይይት መርሐ ግብር የተሳተፉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

መድረኩ የውይይት ግኝቶቹን በማጠናከር የከፍተኛ አመራሩን ትኩረትና መፍትሔ የሚሹ እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ሚናቸውን የሚወጡባቸውን ጉዳዮች በመለየት ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.