የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – አቶ ኡስማን ሱሩር
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ አሉ በክልሉ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር።
አቶ ኡስማን ሱሩር በጉራጌና ስልጤ ዞኖች ከ136 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፍተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ÷ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለያዩ ዘርፎች የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
ለአገልግሎት የበቁት መሰረተ ልማቶች የግብርና ኢኒሼቲቮች ግባቸውን እንዲመቱ በማስቻል ድህነትን ለማሸነፍ ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ አስረድተዋል፡፡
ከተመረቁ ፕሮጀክቶች መካከል ዘመናዊ የእንስሳት ሽያጭ ማዕከላት፣ የወተት ማቀነባበሪያ፣ የህብረት ሥራ ማህበራት መጋዘን፣ ድልድዮች እና የሰብል ግብይት ማዕከላት ይገኙበታል፡፡
በነገዎ ብዙነህ