Fana: At a Speed of Life!

በህንድ በተከሰከሰው አውሮፕላን ለምርመራ ወሳኝ የሆነው የድምጽ መቅጃ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፈው ሳምንት በህንድ የመከስከስ አደጋ ያጋጠመው አውሮፕላን ለምርመራ ወሳኝ የሆነው የድምጽ መቅጃ መገኘቱን የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ የሚገኘው የምርመራ ቡድን አስታውቋል፡፡

ከህንዷ አህመዳባድ ከተማ ተነስቶ ወደ ለንደን በመብረር ላይ የነበረ ቦይንግ 787-8 አውሮፕላን ተከስክሶ አደጋው በተከሰተበት ስፍራ የነበሩትን ጨምሮ 270 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡

የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ የሚገኘው የምርመራ ቡድን በአውሮፕላኑ የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል የሚገኘውን የድምጽ መቅጃ ማግኘቱን ገልጿል፡፡

በበረራው ወቅት የነበረውን የአየር ሁኔታና የአውሮፕላኑን ፍጥነት ጨምሮ የበረራ መረጃዎችን ለመቅዳት የሚያገለግለውና ኤፍ ዲ አር በመባል የሚታወቀው መሳሪያ ባሳለፍነው አርብ መገኘቱ ይታወሳል፡፡

ጥቁር ሳጥን በመባል የሚታወቀው የአውሮፕላኑ ክፍል የድምጽ መቅጃ (ሲቪአር) እና የበረራ መረጃዎች መቅጃ (ኤፍ ዲ አር) የተባሉ ሁለት መሳሪያዎችን በውስጡ የያዘ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡

የጥቁር ሳጥኑ ሁለቱም መሳሪያዎች መገኘት የህንዱ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቡድን ከአሜሪካና እንግሊዝ የባለሙያዎች ቡድን ጋር በትብብር እያከናወነው ላለው ምርመራ ወሳኝ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.