Fana: At a Speed of Life!

በተኪ ምርቶች ለሚሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ አቅርቦት ለማሟላት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተኪ ምርቶች ለሚሰማሩ እና አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችን ለሚተገብሩ ሥራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ አቅርቦትን ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፡፡

የባንኩ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ዋቄ እንዳሉት÷ ተቋሙ በተለያዩ ዘርፎች ለሚሰማሩ አልሚዎች የፋይናንስ አቅርቦትን ከማሳለጥ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡

በተለይም በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በሃይል ማመንጨት እና ሌሎች ዘርፎች ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ፋይናንስ የማቅረብ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ጥረት ለሚያደርጉ ባለሃብቶች አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡

አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችን ወደ ኢኮኖሚ ለማስገባት ጥናት መካሄዱን የገለጹት አቶ ጌታቸው÷ ሃሳቦች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ የሚያስችል አዋጅ ለማስጸደቅ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ፋይናንስ አግኝተው ወደ ሥራ የሚገቡ አልሚዎች የሚወስዱትን ብድር በወቅቱ የመመለስ ችግር በስፋት እንደሚስተዋልባቸው አንስተዋል፡፡

ይህም ባንኩ በሚሰጠው ተደራሽ እና ሁሉን አቀፍ የፋይናንስ አቅርቦት ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ነው ያስገነዘቡት፡፡

ልማት ባንክ በተለያዩ ዘርፎች ምርታማነት ለማሳደግ የሚያሳድግ አስፈላጊ የክሕሎት ሥልጠና ለአምራች ኢንተርፕራይዞች እየሰጠ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

ከ130 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አምራች ኢንተርፕራይዞች የክህሎት ስልጠና መሰጠቱን ጠቅሰው÷ ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

አምራቾች ከመስሪያ ቦታ ጋር ተያይዞ የሚያነሱትን ጥያቄ ለመፍታት ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በትኩረት እንዲሰሩም ጠይቀዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.