Fana: At a Speed of Life!

የኢራን መሪ የት እንዳሉ ብናውቅም አሁን ላይ እንዲገደሉ አንፈልግም – ፕሬዚዳንት ትራምፕ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሀሚኒ የት እንደተደበቁ እንደሚያውቁና ቢያንስ አሁን ላይ እሳቸውን ለመግደል እንደማይፈልጉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኢራኑ መሪ በትክክል የት እንዳሉ እናውቃለን ያሉ ሲሆን ነገር ግን አሁን ላይ እንዲገደሉ ፍላጎት የለንም ብለዋል፡፡
ነገር ግን በንጹሃን ላይ ብሎም በአሜሪካ ወታደሮች ላይ የሚሳኤል ጥቃት እንዲፈጸም አንፈልግም ነው ያሉት፡፡
ትዕግስታችን እየተሟጠጠ ነው በማለት በትሩዝ የማህበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
አምስት ቀናት ያስቆጠረው የእስራኤልና ኢራን ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ እየተገለጸ ይገኛል፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.