Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን ትንሳኤ የምናረጋግጠው ሌት ተቀን በመስራት ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ትንሳኤ የምናረጋግጠው ሌት ተቀን በመስራት ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማ ዞን የከተማ እና የገጠር ኮሪደር ልማት ስራዎችን፣ የአባ ጅፋር ቤተመንግስት ዕድሳትና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የጅማን የቀደመ ታሪክ የበለጠ የሚያደምቅ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ ገልጸው፥ የትናንቱን የጅማ ዕሴት የሚጠብቁና የነገውን ዘመን የሚዋጁ አስደናቂ ሥራዎች ዕውን እየሆኑ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

‎በዞኑ ማና ወረዳ የቡና፣ የሻይ ቅጠል፣ የማርና ሌሎች የልማት ስራዎችን እንዲሁም በገጠር ኮሪደር ለሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ሞዴል የሆነና ተግባር ተኮር ስራን በማየቴ ኩራት ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡

‎የኢትዮጵያን ትንሳኤ የምናረጋግጠው ሌት ተቀን በመስራት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የደረስንበትና ያገኘነው ውጤት ሳያዘናጋን ለነገ ሰፊ የመልማት ጸጋችን የቀጠለ ትጋት ያስፈልጋል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

‎እንደ ሀገር እየተከልነው ያለነው ልማትን ጀምሮ የመጨረስ ባህላችን የሚጨበጥ፣ በተግባር የታየ አብነትና ለነገ የሚሻገር አሻራ ነው ብለዋል፡፡

ጅማ ይሄን ዕውን ለማድረግ ትልቅ ትግል ላይ ሆና በማየታቸው መደሰታቸውንም ነው አቶ ተመስገን ጥሩነህ የገለጹት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.