አመራሩ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የተመዘገበውን ውጤት ሊያስቀጥል ይገባል – አቶ ጥላሁን ከበደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አመራሩ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የተመዘገበውን ውጤት አጠናክሮ ሊያስቀጥል ይገባል አሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ።
የክልሉ የመንግስት እና የፓርቲ 90 ቀናት አፈፃፀም እና የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በውይይት መድረኩ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት፤ ሕዝቦችን ለልማትና ለውጥ በሚያነሳሳ ትርክት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።
ከመጋቢት እስከ ግንቦት ድረስ የተሰሩ የልማት፣ የሠላምና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ተግባር መከናወኑን አንስተዋል።
የተቀረጹ ኢኒሼቲቮችም ሕዝቡን በማሳተፍ መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ውጤት እያመጡ እንደሆነ ተናግረዋል።
የእርሻ ስራ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ ዜጎችን ከተረጂነት ማላቀቅ እንዲሁም የክረምትና በጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ እንደሆነ ጠቁመዋል።
67 ሺህ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ገበያ በማረጋጋት፣ በከተሞች ውበት፣ በኮሪደር ልማት፣ በትምህርት ለትውልድ መርሐ ግብር፣ በጤና ልማት እና በገቢ አቅም ማሳደግ በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በኮደርስ ስልጠና፣ በፋይዳ መታወቂያ ስርጭት፣ በኮንትሮባንድ መከላከል፣ ቱሪዝምን በመደገፍ፣ እንዲሀም የሲቪል ሰርቪስና የፍትህ ማሻሻያ፣ ሠላም እና ደህንነት ሰፊ ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል።
ፈተናዎችን መቋቋም የሚያስችል ብቃት ያለውን አመራር መፈጠሩን ጠቅሰው፤ አመራሩ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የተመዘገበውን ውጤት አጠናክሮ ሊያስቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በበኩላቸው፤ ‘ከተሰጠን በላይ መስራት ከሚጠበቅብን በላይ መፈጸም’ በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው የ90 ቀናት እቅድ በስኬት ተጠናቅቋል ብለዋል።
በመለሰ ታደለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!