ዓለም አቀፍ የልማት አጀንዳዎች ከብሔራዊ እቅዶች ጋር ተጣጥመው እየተተገበሩ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ የልማት አጀንዳዎችን ከብሔራዊ እቅዶች ጋር አጣምራ መተግበሯን አጠናክራ ትቀጥላለች አለ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፡፡
ላላፉት ሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ የግምገማ ማህበር 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ተጠናቅቋል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ጥሩማር አባተ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የተካሄደው መርሐ ግብር እንግዶችን በማስተናገድና ኹነቶችን በማካሄድ ስኬታማ ነው።
የምዘና ሥርዓትን ለማጠናከር የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለመስጠት፣ የሀገራት ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥና ትብብርን ለማጠናከር የተያዘውን ግብን ለማሳካት እንደተቻለ አብራርተዋል።
ሀገራት እንደየነባራዊ ሁኔታቸው የሚከተሉትን የምዘና ሥርዓት በመድረኩ ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን÷ ኢትዮጵያም ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ሥርዓትን ለመዘርጋት ያከናወነቻቸውን ተግባራት ማቅረቧን ተናግረዋል።
አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የልማት እቅዶችን ከብሔራዊ እቅዶቿ ጋር በማጣመርና የትግበራ ሒደታቸውን ሪፖርት፣ ክትትልና ግምገማ በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ እየተገበረች የምትገኘው የ10 ዓመት የልማት እቅድ አጀንዳ 2063 እና የዘላቂ ልማት ግቦችን አጣምሮ የያዘ መሆኑ አስታውሰው÷ በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።
የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ተወካይ አምባሳደር ሞሃመድ ኢልአሚኒ በበኩላቸው÷በአህጉሪቷ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔ በመስጠት እንዲሁም አፈጻጸሙን ክትትል በማድረግ ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአፍሪካ የግምገማ ማህበር በአጀንዳ 2063 ትግበራ በትብብር መስራቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀው ÷ ሀገራት ለአቅም ግንባታ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።
የአፍሪካ ግምገማ ማህበር ፕሬዚዳንት ሚቼ ኦዲራጎ ÷ ባለፉት ሶስት ቀናት በአፍሪካ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔ መስጠት የሚያስችል የግምገማ ሥርዓትንና ትብብርን የሚያጠናክሩ ሁነቶች መካሄዳቸውን ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!