Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 37 ሺህ ቶን የተቀነባበረ መኖ አመረተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 በጀት ዓመት 10 ወራት 37 ሺህ ቶን የተቀነባበረ መኖ አመረተ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት፤ የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን ውጤታማ የሚያደርጉ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል።

ከእነዚህ ተግባራት መካከል የእንስሳት መኖ ልማት መሆኑን በመግለጽ፤ ጥራቱን የጠበቀ የእንስሳት መኖ በበቂ መጠን ለማቅረብ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።

በእንስሳት እርባታ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎችም የጓሮ እርጥብ መኖ ምርታማነትም አድጓል ብለዋል።

የተለያዩ ቤተሰብ ተኮር የመኖ ልማት ኢኒሼቲቮች ተቀርፀው በመተግበር ውጤታማ እየሆነ መጥቷል ነው ያሉት።

በክልሉ የተለያየ መጠን ባለው ስፍራ መኖ ለማልማት የሚያስችል ኢኒሼቲቭ በመቅረጽ በዓመት ከአራት ጊዜ በላይ በማምረት ፍላጎትን ከማሟላት ባለፈ መኖ ለገበያ ማቅረብ የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል።

በተጨማሪም በክልሉ ከ14 በላይ የመኖ ማቀነባበሪያ ህብረት ስራ ማኅበራት እና የተደራጁ ወጣቶች መኖራቸውን አንስተው÷ የተማሩ ወጣቶች ተደራጅተው የመኖ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች እንዲፈጥሩ ለማስቻል እየተሰራ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የመኖ ልማት ሥራ እንስሳትን ከመመገብ ባለፈ የአፈር ለምነትን በማልማት፣ በመጠበቅና አፈርና ውሃ እቀባን ለማሻሻል የጎላ አስተዋጽዖ እንዳለውም ነው ያብራሩት።

መኖ ለእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ውጤታማነት ትልቅ ሚና እንዳለው የገለጹት አቶ ኡስማን÷ በበልግ፣ መስኖ እና ቅድመ መስኖ ወቅቶች ላይ መኖ እየለማ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ባለፉት 10 ወራት ከ45 ሺህ ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ መኖ መልማቱን እና 37 ሺህ ቶን የተቀነባበረ መኖ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.