Fana: At a Speed of Life!

ኢራን በአሜሪካ ለተፈጸመባት ጥቃት አጸፋዊ ርምጃ እወስዳለሁ አለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢራን በሦስት የኒውክሌር ማዕከላት ላይ አሜሪካ ለፈጸመችባት ጥቃት የአጸፋ ርምጃ ለመውሰድ ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ ናቸው ስትል አስጠንቅቃለች።
አሜሪካ ከሰዓታት በፊት ግዙፉን ፎርዶው የኒውክሌር ተቋም ጨምሮ በሦስት የኢራን ኒውክሌር ማዕከላት ላይ የተሳካ የቦምብ ድብደባ መፈጸሟን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።
የአሜሪካን የቦምብ ጥቃት አስደንጋጭ ሲሉ የገለጹት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ፥ ጥቃቱ ዘላለማዊና የማያባራ ጥፋት ያስከትላል ብለዋል።
ሀገራቸው ልዑላዊነቷን ለመከላከል በአሜሪካ ላይ የአጸፋ ርምጃ ለመውሰድ ሁሉንም አማራጮች ትመለከታለች፤ አማራጮችም በጠረጴዛ ላይ ናቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
አሜሪካ በፎርዶው፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ ከፈጸመችው የቦምብ ጥቃት በኋላ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሰጡት መግለጫ ፥ ኢራን በፍጥነት ወደ ሰላም መምጣት አለባት ብለዋል፡፡
ኢራን ወደ ሰላም የማትመጣ ከሆነ በቀጣይ ሌሎች ኢላማዎች ላይ ከፍ ያለ ጥቃት እንፈጽማለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.