Fana: At a Speed of Life!

የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መንግስታቸው ስልጣን መልቀቁን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሳን ዲያብ መንግስታቸው በራሱ ፍቃድ ስልጣን መልቀቁን አስታወቁ።

ባሳለፍነው ሳምንት ማክሰኞ በዋና ከተማዋ ቤሩት በደረሰው ፍንዳታ በርካታ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ነው።

ይህንን ተከትሎም በፍንዳታው የተናደዱ ሊባኖሳውያን አደባባይ በመውጣት ለተከታታይ ቀናት በሀገሪቱ መንግስት ላይ ቁጣቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

በተቃውሞ ላይ የሚገኙ የሀገሪቱ ዜጎች አሁን ያለው የመንግስት አመራሮች በሙስና ተጠምደው የሀገሪቱን ዜጎች ረስተዋል፤ በመንግስት መዘናጋት ነው ፍንዳታው የደረሰው ሲሉም ይወቅሳሉ።

በመንግስታቸው ላይ ተቃውሞ የበረታባቸው የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን ዲያብ ትናንት ምሽት በሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቀርበው ካቢኔያቸው በሙሉ በራሱ ፍቃድ ስልጣን መልቀቁን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን ዲያብ የመንግስታቸው ስልጣን መልቀቅ ደብዳቤንም ለሊባኖሱ ፕሬዚዳንት ሚሼል አውን አስረክበዋል።

መልቀቂያውን የተቀበሉት ፕሬዚዳንቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን ዲያብ ካቢኔ አዲስ መንግስት እስኪመሰርት ድረስ በባላደራ መንግስትነት ስልጣን ላይ እንዲቆይ ጠይቀዋል ነው የተባለው።

ባሳለፍነው ሳምንት በሊባኖሷ ቤሩት የደረሰው ፍንዳታ የተከሰተው ጥንቃቄ በጎደለው መንገድ ለበርካታ ዓመታት በተከማቸ 2 ሺህ 750 ቶን የሚመዝን አሞኒዬም ናይትሬት በተባለ ንጥረ ነገር እንደሆነ ተነግሯል።

በቤሩቱ ፍንዳታ ምክንያትም ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ቁጥር 220 መድረሱን እና 110 ሰዎች ደግሞ የገቡበት እንደማይታወቅ እንዲሁም ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

ምንጭ፦ bbc.com

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.