ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውድድር ዓመቱን በአቻ ውጤት አጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ36ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 ለ 2 አቻ ተለያዩ፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ግቦች እስራኤል ሸጎሌ እና ዮሀንስ ኪዳኔ ሲያስቆጥሩ፥ ወልደአማኑኤል ጌቱ እና ኪቲካ ጅማ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኳስና መረብን አገናኝተዋል፡፡
ሁለቱ ክለቦች በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ ነጥብ መጋራታቸውን ተከትሎ፥ ኢትዮጵያ ቡና በ60 ነጥብ 2ኛ እንዲሁም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ44 ነጥብ 10ኛ ሆነው የውድድር አመቱን አጠናቅቀዋል፡፡