Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪዎችን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የሃይል አቅርቦት ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፡፡

የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን እንዳሉት÷ የገፈርሳ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን አቅም ለማሳደግ የተተከለው አዲስ ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

ወደ ሥራ የገባው ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት ተንቀሳቃሽ የኃይል የማከፋፈያ የጣቢያውን አቅም ወደ 200 ሜጋ ዋት ያሳድጋል ብለዋል፡፡

ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው በአካባቢው ይስተዋል የነበረውን የኃይል መቆራረጥ ችግር እንደሚያስቀር አንስተዋል፡፡

በየአካባቢው እያደገ የመጣው የተጨማሪ ኃይል ፍላጎት ከጣቢያው አቅም በላይ እንዲሆን በማድረጉ አዲስ ተንቀሳቃሽ የሃይል ማከፋፈያ ጣብያ መተከሉን አቶ ሞገስ ለፋና ሚድያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

የተንቀሳቃሽ ጣቢያ ተከላ የሚከናወነው ኃይል ፈላጊ አካባቢዎች የራሳቸው ቋሚ ማከፋፈያ እስኪያገኙና በነባር ማከፋፈያዎች ላይ የአቅም ውስንነት ሲያጋጥም ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

በተለይ ኢንዱስትሪዎች ለሚፈልጉት የማስፋፊያ እና የማምረት አቅም ለማሳደግ እንደሚያግዝ ጠቁመው÷ በቀጣይ የኢንዱስትሪዎችን የሃይል ፍላጎት ለማሳካት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

የገፈርሳ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ባሉት ስድስት መስመሮች ለአዲስ ዓለም፣ ፍቼ፣ ሙገር ሲሚንቶ፣ ጊንጪ፣ ጌዶ፣ ሰበታ እና ሸጎሌ ኃይል ሲያሰራጭ ቆይቷል፡፡

በትዕግስት አብርሃም

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.