Fana: At a Speed of Life!

ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ36ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ በውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታውን በድል ቋጭቷል፡፡

የወላይታ ድቻን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቴዎድሮስ ኃይለማርያም ሲያስቆጥር፥ ድሉን ተከትሎ ክለቡ 48 ነጥብ በመያዝ መርሐ ግብሩን አጠናቅቋል፡፡

43 ነጥብ በመያዝ የውድድር ዓመቱን ያጠናቀቀው ድሬዳዋ ከተማ ባለፈው ሳምንት ስሑል ሽረን በማሸነፍ በሊጉ መሰንበቱን ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ በቡጣቃ ሸመና ብቸኛ ግብ ሀድያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.