ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ ቁርጠኝነት የሚታይበት የመገጭ መስኖ ግድብ…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ለፍጻሜ የማብቃት ቁርጠኝነትን በሚያሳይ መልኩ እየተከናወነ ነው፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት ያደረጉ የሕዝብ እና የግል ሚዲያዎች እንዲሁም የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ በዚሁ ወቅት ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ መንግሥት የተለያዩ ፈተናዎችን በመቋቋም ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እያበቃ ይገኛል።
አዳዲስና ቀደም ሲል ተጀምረው ሲጓተቱ የነበሩ ፕሮጀክቶች በልዩ ትኩረት በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቁ እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።
ከዓመታት በፊት ተጀምረው ሲጓተቱ ከነበሩ ፕሮጀክቶች መካከል ከ17 ዓመታት በፊት ግንባታ የተጀመረው የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት ይጠቀሳል፡፡
ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት በፍጥነት እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
በዚህም አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ መንግሥት ፕሮጀክቶችን ለፍጻሜ ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ በበኩላቸው፥ አስተዳደሩ ለፕሮጀክቱ ፍጻሜ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በዐቢይ ጌታሁን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!