በደብረ ብርሃን ከተማ አንዲት እናት አራት ልጆችን በሰላም ተገላገለች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው ሃኪም ግዛው ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን በሰላም ተገላግላለች።
በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪም ዶ/ር አዲሱ ግርማ የ38 ዓመቷ እናት የባሶና ወራና ወረዳ መምጣቷን ገልጸው÷ በህክምና ባለሙያዎች በተደረገላት እገዛ አራት ሴት ልጆችን በሰላም መገላገሏን ተናግረዋል፡፡
በሆስፒታሉ ታሪክ አንዲት እናት አራት ልጆችን ስትገላገል ይህ የመጀመሪያው ነው ያሉት ዶ/ር አዲሱ÷ ሁሉም ህጻናት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ህጻናቱ ከ1 ነጥብ 3 ኪሎ ግራም እስከ 1 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም ክብደት እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡
እናታቸውም ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት የወለዷቸው አራት ወንድ እና ሁለት ሴት በአጠቃላይ ስድስት ልጆች እንዳሏቸው አስታውሰው÷ አሁን ደግሞ አራት ልጆችን በአንድ ጊዜ በመውለዳቸው ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
አቅም ያላቸው በጎ አድራጊዎች ልጆቻቸውን ለማሳደግ የሚያስችል ድጋፍ እንዲያደርጉላቸውም ጠይቀዋል።
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሃኪም ግዛው ሆስፒታል ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሕብረተሰቡ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
በሰላም አሰፋ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!