አዳማ ከተማ ከፕሪሚየር ሊጉ ወረደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ36ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ በሀዋሳ ከተማ ተሸንፎ ከፕሪሚየር ሊጉ ወርዷል፡፡
ዛሬ 9፡00 ላይ የተደረገው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የሀዋሳ ከተማን ግቦች አቤኔዘር ዮሐንስ እና በረከት ሳሙኤል ሲያስቆጥሩ፥ አዳማ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ቢኒያም አይተን ከመረብ አሳርፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ በ39 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አዳማ ከተማ፥ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ተከትሎ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ተረጋግጧል፡፡
የአዳማ ከተማን መሸነፍ ተከትሎ በሊጉ መሰንበቱን ያረጋገጠው ፋሲል ከነማ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡናን ይገጥማል፡፡