በክልሉ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የጤና ተቋማት ግንባታ እየተከናወነ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ700 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የጤና ተቋማት ግንባታና ማስፋፊያ እየተከናወነ ይገኛል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ የጤና ተቋማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥና አገልግሎቱን ለማሻሻል ከ97 በላይ አዲስ የጤና ተቋማት ግንባታ፣ ጥገናና ማስፋፊያ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡
የፕሮጀክቶቹ ግንባታና ማስፋፊያ ስራ በመንግስት፣ ህብረተሰብ፣ ባለሃብቶች እንዲሁም አጋር አካላትን በማስተባበር እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም ከ241 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የክልሉ መንግስት ለፕሮጀክቶች መመደቡን አንስተው÷ ከ497 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ በህብረተሰብ፣ ባለሃብት እና አጋር አካላትን በማስተባበር በድምሩ 738 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ፕሮክቶቹ እየተሰሩ መሆናቸውን ነው ያስረዱት።
ፕሮጀክቶቹም ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ አጠቃላይ ጤና ኬላዎች፣ መሰረታዊ ጤና ኬላዎች፣ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶች እና የጤና ተቋም ማስፋፊያዎች ናቸው፡፡
በግንባታ ላይ ከሚገኙት ፕሮጀክቶች ውስጥ በቀድሞው ደቡብ ክልል ግንባታቸው የተቋረጡ እንደሚገኙበት አመልክተዋል፡፡
አሁን ላይ ሁሉም የግንባታ ፕሮጀክቶች የነበሩባቸውን ችግሮች በመቅረፍ በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተከናወኑ እንደሚገኙ አቶ ሳሙኤል አብራርተዋል፡፡
ከፕሮጀክቶቹ መካከል ግንባታቸው ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት የጀመሩትን ጨምሮ በበጀት ዓመቱ 44 የግንባታ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ርክክብ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የጤና ተቋማትን ለማስፋፋትና አገልግሎትን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑንም አውስተዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!