Fana: At a Speed of Life!

ኢራን ከሞሳድ ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን ከ700 በላይ ዜጎች አሰረች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢራን ከእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን ከ700 በላይ ዜጎች ማሰሯ ተነገረ፡፡

ባለፉት 12 ቀናት ብቻ ኢራን ከ700 በላይ ዜጎችን ከእስራኤል ጋር ግንኙነት በመፍጠር እያሴሩ ነው በሚል ጥርጣሬ ማሰሯን ፋርስ የዜና ወኪልን ዋቢ አድርጎ የዘገበው አርቲ ነው፡፡

በተጨማሪም ለእስረኤል ሲሰልሉ ተገኙ የተባሉ ሶስት ዜጎች በዛሬው እለት መገደላቸው ተሰምቷል፡፡

በሌላ ዜና የኢራን የኒውክለር ማመንጫ ጣቢያ ፎርዶው በአሜሪካ ቡንከር ቡስተር ቦምብ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል ሲሉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትርምፕ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት ኢራን በኒውክለር ጣቢያው ላይ ምንም አይነት የከፋ ጉዳት አለመድረሱን መግለጧን ተከትሎ ነው፡፡

እስራኤል በጉዳዩ ላይ መረጃ እንዳሰባሰበች የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፥ በዚህም አሜሪካ ጥቃት የፈጸመችባቸው የኒውክለር ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ኢራን የኒውክለር ፕሮግራሟን ዳግም የምትጀምር ከሆነ አሜሪካ ዳግመኛ እርምጃ ትወስዳለች ነው ያሉት፡፡

በአቤል ነዋይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.