ባህር ዳር ከተማ 3ኛ ደረጃን ይዞ የውድድር ዓመቱን አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ36ኛ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የባህርዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ሙጂብ ቃሲም፣ በረከት ጥጋቡ እና ይሄነው የማታው አስቆጥረዋል፡፡
ባህር ዳር ከተማ 54 ነጥብ በመሰብሰብ 3ኛ ደረጃን በመያዝ የውድድር ዓመቱን አጠናቅቋል፡፡
አስቀድሞ ከሊጉ የወረደው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ካደረጋቸው 34 ጨዋታዎች 19 ነጥብ በመሰብሰብ 18ኛ ደረጃን በመያዝ የውድድር ዓመቱን ቋጭቷል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ መቐለ 70 እንደርታ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከጨዋታው አንድ ነጥብ ማግኘት ከቻለ ከተጋጣሚው መቐለ 70 እንደርታ በግብ ክፍያ በመብለጥ በፕሪሚየር ሊጉ መቆየቱን ያረጋግጣል፡፡
መቐለ 70 እንደርታ በአንጻሩ ከሊጉ ላለመውረድ ማሸነፍን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡