Fana: At a Speed of Life!

የሀሳብ ልዩነቶችን በምክክር የመፍታት ባህልን ለማዳበር የሃይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው – ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀሳብ ልዩነቶችን በንግግርና በምክክር የመፍታት ባህልን ለማዳበር የሃይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው አሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሚሽነር ሞሃሙድ ድሪር።

በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አዘጋጅነት “ለስኬታማ ሀገራዊ ምክክር የሃይማኖት ምሁራን ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ ኮሚሽነር ሞሃመድ ድሪር እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ሰብዓዊነትን፣ መከባበርን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን በማስተማር የሀገር አንድነትን በጽኑ አቁመዋል።

የሃይማኖት ተቋማት በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ የነበራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ነው ያነሱት።

የሃይማኖት ተቋማት ጊዜና ትኩረታቸውን በመስጠት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሊመከርባቸው ይገባል ያሉትን አጀንዳ በመስጠት ታሪክ የማይሽረውን ገድል መፈጸማቸውንም ተናግረዋል።

የግጭት አዙሪትን በማስቀረትና የሀሳብ ልዩነቶችን በንግግርና በምክክር የመፍታት ባህልን ለማዳበር የሃይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው÷ ተቋማቱ የቤት ስራቸውን በአግባቡ በመወጣት ለጠንካራ ሀገር ግንባታ በይበልጥ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

ከተሳተፊ ልየታ ጀምሮ ንቁ ተሳትፎ እንደነበራቸው በማንሳት በቀጣይ ምዕራፍም ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

በአቤል ነዋይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.