Fana: At a Speed of Life!

ሀይደር ሸረፋ የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት የመዝጊያ መርሐ ግብር በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዳል።

በ18 ክለቦች ለ36 ሣምንታት ሲደረግ የቆየው የፕሪሚየር ሊጉ ውድድር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የዓመቱን ምርጦች በመሸለም ነው የመዝጊያ መርሐ ግብሩ የተካሄደው።

በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ መድኑ ሀይደር ሸረፋ የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ኮኮብ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል።

በዚህም ተጨዋቹ ከምንያህል ተሾመ በመቀጠል ከተለያዩ ሦስት ክለቦች ጋር የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ያሸነፈ ተጫዋች ሆኗል።

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ተስፈኛ አዳጊ ተጫዋች ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናው ይታገሱ ታሪኩ ሆኖ ሲመረጥ÷ በምርጥ ግብ ጠባቂ ዘርፍ የኢትዮጵያ መድኑ አቡበከር ኑራ አሸንፏል።

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ገብረመደህን ኃይሌ በመሆን ሲያሸንፍ÷ የሀዋሳ ከተማው የፊት መስመር ተጫዋች አሊ ሱሌማን በ21 ግቦች የሊጉ ከፍተኛ ግብ አሰቆጣሪ ሆኖ አጠናቅቋል።

በፕሪሚየር ሊጉ ምስጉን ዋና ዳኛ ማኑኤል ወልደፃዲቅ እና ምስጉን ረዳት ዳኛ ሙስጠፋ መኪ ሆነው ተመርጠዋል።

በእንዳልካቸው ወዳጄ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.