Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለችግኝ መትከያ የሚሆን ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን በላይ ጉድጓድ ተዘጋጅቷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ለሚካሄደው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ።

የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ በክልሉ ለዘንድሮው መርሀ ግብር 1 ነጥብ 62 ቢሊየን ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ 1 ነጥብ 55 ቢሊየን ማሳካት ተችሏል።

በክልሉ ከ200 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መዘጋጀቱን ጠቁመው፤ በችግኝ ተከላው ህብረተሰቡ በስፋት እንደሚሳተፍ ጠቁመዋል።

በመርሃ ግብሩ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የጥምር ደን ችግኞች እንደሚተከሉም ነው የገለጹት።

በዚህም የደን፣ የመኖ፣ የፍራፍሬ እና የአፈር ለምነትን የሚጠብቁ እዕዋት እንደሚተከሉ ገልጸው፤ እስካሁን ከ1 ነጥብ 2 በሊዮን በላይ የችግኝ መትከያ ጉድጓድ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

በከድር መሀመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.