ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ የቤተክርስቲያኒቷ አባቶች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
ብጹዓን አባቶቹ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ያካሄዱት በአዲስ አበባ ቦሌ ቪአይፒ ተርሚናል አካባቢ ነው።
በችግኝ ተከላው ወቅት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአረንጓዴ አሻራ የላቀ አበርክቶ እያደረገች መሆኗን ተናግረዋል።
ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት አረንጓዴ አሻራቸውን ማኖር የሚችሉበት ስፍራ በአስተዳደሩ ተለይቶ መዘጋጀቱን ገልጸው፤ ምዕመኑ በንቃት ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በዙፋን ካሳሁን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!