Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 13ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በአራት ወሳኝ ከተማ አቀፍ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

የከተማዋን ፈጣን ለዉጥ ታሳቢ በማድረግ፣ ወጪን ለመቀነስ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና ውጤታማነትን ለማሳደግ እንዲረዳ ተጠንቶ የቀረበዉ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር የማሻሽያ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለምክር ቤት እንዲቀርብ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም መሠረት ቱሪዝም ዘርፍ ራሱን ችሎ በኮሚሽን እንዲቋቋም፣ የዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ እና የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅ/ቤት እንዲዋሃዱ፣ ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ፅ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር እንዲዋሃድ ወስኗል።

እንዲሁም የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን የማልማት ተግባር ለውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ማስተላለፍን ያከተተ ማሻሻያዎች ተደርገዉ ለምክር ቤት እንዲቀርብ ወስኗል።

ለአስተዳደራዊ አመቺነት፣ ለአገልግሎት ተደራሽነት እና ወጪን ለመቀነስ እንዲያግዝ በፕላን ልማት ቢሮ ተጠንቶ በቀረበዉ የሶስት የወረዳዎች አስተዳደር ወሰን ማሻሻል ጥናት ላይ ተወያይቶ አገልግሎት ተደራሽነትን እና ወደፊት በከተማዋ የሚመጣውን ልማት ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ የቀረበውን የማሻሻያ ሀሳብ ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

በጤና ቢሮ በኩል ተጠንቶ በቀረበዉ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላት ክፍያ መጠን ላይ በመወያየትም ውሳኔ ማሳለፉን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

በመጨረሻም ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ፕሮጀክቶች ላይ የቀረበ የመሬት ልማት ጥያቄ ላይ ካቢኔው በመወያየት አጽድቋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.