Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት በጎርፍ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት በትናንትናው ዕለት በደረሰ የጎርፍ አደጋ 24 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ሰዎች መጥፋታቸው ተነግሯል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አደጋውን አስደንጋጭ ያሉ ሲሆን፥ ለነፍስ አድን ስራው አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡

የጎርፍ አደጋው በደረሰበት ጓዳሉፕ በተባለ ወንዝ አቅራቢያ በሚገኝ የሴቶች ካምፕ ውስጥ የነበሩ ታዳጊዎች መጥፋታቸውን የግዛቲቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች የጎርፍ አደጋውን ተከትሎ የጠፉ ሰዎችን ለማትረፍ ርብርብ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.