ከሕዳሴ ግድብ 5 ሺህ 895 ቶን የዓሣ ምርት ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚገኘውን የዓሣ ምርት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ።
በቢሮው የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዳይሬክተር አቶ ሃይሉ ይርጋ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ የሌማት ትሩፋት በክልሉ የዓሣ ሃብት ልማትን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡
የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በዓመት 15 ሺህ ቶን ዓሳ ማምረት የሚያስችል አቅም በክልሉ እንዳለ በጥናት መለየቱን አመልክተዋል፡፡
የፊታችን መስከረም ወር ላይ የሚመረቀው የሕዳሴ ግድብ ለዓሣ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
በግድቡ ሰው ሠራሽ ሐይቅ ለሚከናወነው የዓሣ ልማት ሥራ አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 849 ወጣቶች በ35 የዓሣ መንደሮች መደራጀታቸውን ጠቅሰው÷ ከእነዚህ መካከልም 547ቱ ወደ ሥራ ገብተው ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ለማህበራቱ በዓሣ ማስገሪያ መረብና በዓሣ ምግብ አሰራር እንዲሁም ዓሣ የማስገር ክህሎት እንዲያዳብሩ የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመዋል።
ከተለያዩ አካላት በተገኘ ድጋፍም ለዓሣ ማስገሪያ የሚውሉ 54 ጀልባዎችና 1 ሺህ 600 መረቦችን ማቅረብ መቻሉን አብራርተዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመትም ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሐይቅና ሌሎች 5 ሺህ 895 በላይ ቶን በላይ የዓሣ ምርት መመረቱን ጠቅሰዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!