በመዲናዋ የተገነቡ 21 ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ 31 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችና 8 ድልድዮች በአጠቃላይ 21 ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የከተማዋ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድርን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት፥ ከተማችንን ለማዘመን ከኮሪደር ልማት ሥራዎቻችን ባሻገር የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ዛሬ ከተመረቁት የመንገድ መሰረተ ልማቶች መካከል ከአጉስታ – ወይራ መጋጠሚያ፣ ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ፣ ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ ዐደባባይ – በአቃቂ ድልድይ – ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ፣ የተገነቡ መንገዶች ይገኙበታል።
ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ መሆኑን የከተማዋ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል።
በኃይለማርያም ተገኝ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!