የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም ልዩነት አያግድም – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለም ልዩነት አያግድም አሉ።
ኢዜማ “በሀሳብ እንፎካከራለን፤ ስለሀገር እንተባበራለን” በሚል መሪ ሀሳብ ከሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊ የሥራ ኃላፊዎችና አባላትም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሸገር ፓርክ ውስጥ ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
በዚሁ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)÷ የፖለቲካ ባህላችን በዜጎች ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገር ይኖርበታል ብለዋል።
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ከመወነጃጀል የጸዳ የፖለቲካ ባህልን በመገንባት በሀገር ጉዳይ ላይ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ርዕዮተ-ዓለማዊ የሃሳብ ልዩነት ተጠባቂና ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው ያሉት ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)÷ ይህም የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በትብብር ከመስራት አያግድም ነው ያሉት።
ኢዜማ የፖለቲካ ርዕዮተ-ዓለማዊ የሃሳብ ልዩነት ሳይገድበው ከገዥው ፓርቲ ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው፤ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ብሔራዊ ጥቅምና በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር እንዲኖረው በትብብር መስራት እንደሚኖርባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢዜማ ሥራ አስፈፃሚ አባል ግርማ ሰይፉ በበኩላቸው÷ ፓርቲው የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ወደሰለጠነ ምዕራፍ ለማሸጋገር ገንቢ ሚናውን እየተወጣ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያዊያንም በሀገራቸው ጉዳይ ከሚፎካከሩባቸው ይልቅ የሀገራቸውን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ የሚተባበሩባቸው በርካታ አጀንዳዎች እንዳሏቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የሚያጋጥማትን ጫና ለመቀነስ ኢትዮጵያ እየሰራችበት የሚገኝ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የልማት አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!