Fana: At a Speed of Life!

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ 79 ከመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እየተገነባ የሚገኘው የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ አፈጻጸም 79 በመቶ ደርሷል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሸ ዋጌሾ (ዶ/ር) ከሌሎች የፌደራልና ክልል ኃላፊዎች ጋር በመሆን አውሮፕላን ማረፊያውን የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል።

በዚሁ ወቅት እንደተገለጸው፥ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው የቆረጣና ሌሎች ስራዎች ተጠናቅቀው የአስፖልት ማንጠፍ ስራ ተጀምሯል፡፡

በአሁኑ ወቅት የግንባታው አፈጻጸም 79 በመቶ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፥ በመጪው ታህሳስ ወር ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚጀምር ይጠበቃል።

ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የግንባታውን ቀሪ ስራዎች ለማጠናቀቅ ለወሰን ማስከበር ለሚያስፈልገው የካሳ ክፍያ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ስራውን ለማጠናቀቅ ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር የብድር አቅርቦት እንዲመቻች አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

ቀሪ የቴክኒክ ስራዎች በአግባቡ ተሰርተው ግንባታውን ከታህሳስ ወር በፊት ለማጠናቀቅ እንዲሰራም ነው ሚኒስትሩ ያሳሰቡት፡፡

በተስፋየ ምሬሳ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.