የሶማሌ ክልል 18 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል በበጀት ዓመቱ 18 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ሰብስቧል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዲ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የክልሉን ገቢ የመሰብሰብ አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ ሰፊ ተግባራት ተከናውኗል።
በዚህም በበጀት ዓመቱ 17 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 18 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ ከዕቅድ በላይ 105 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በበጀት ዓመቱ የተሰበሰበው ገቢ ከ2016 ዓ.ም አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ጋር የ36 ነጥብ 5 እድገት እንዳለውም ነው የተናገሩት።
በዮናስ ጌትነት